Translation

‘እጅግ በጣም አስቸኳይ ፍላጎት’: ረሃብ ትግራይን እያስጨነቀ ነው

Published

on

በካራ አና ተፅፎ በ Horn Anarchists ተተረጎመ ናይሮቢ፣ ኬንያ 

    እጅግ ከደከሙ ስደተኞች፣ በአጨዳ ወቅት አፋፍ ላይ እስከ ተቃጠሉ ሰብሎች ድረስ ረሃብ በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ውስጥ ከሁለት ወር በላይ ከዘለቀው ጦርነት በህይወት መትረፍ ለቻሉት ትልቅ ስጋት ጋርጦባቸዋል፡፡

ሰብአዊ እርዳታን ለማዳረስ የኢትዮጵያ መንግሥትን ተማፅነው ከገቡት የመጀመሪያ ግብረ ሰናይ ሠራተኞች ከወንዞች ውሃ እየጠጡ ስለተዳከሙ እና በተቅማጥ እየሞቱ ስላሉ ሕፃናት ይገልፃሉ፡፡ ሱቆች ከሳምንታት በፊት ተዘርፈው አልቀዋል፡፡ አንድ የአካባቢው ባለሥልጣን ታህሳስ 23 ቀን በተደረገ የመንግሥት እና የእርዳታ ሠራተኞች ስብሰባ ላይ እንደተናገሩት የተራቡ ሰዎች “አንዲት ብስኩት” ጠይቀዋል፡፡ ከ 4.5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ፣ የክልሉ ጠቅላላው ህዝብ ቁጥር ለማለት በሚያስችል ሁኔታ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ይስፈልጋቸዋል ሲሉ የስብሰባው ተሳታፊዎች ተናግረዋል፡፡ አንድ የትግራይ አስተዳዳሪ ታህሳስ 30 ቀን ባደረጉት ስብሰባ ላይ ያለ እርዳታው ባፋጣኝ ካልደረሰ “በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በረሃብ ሊሞቱ ይችላሉ” ሲሉ አስጠንቅቀው ነበር አሶሺዬትድ ፕሬስ ያገኛቸው ቃለ ጉባኤዎች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች በረሃብ መሞት እንደጀመሩ ያመለክታል፡

የዶክተርስ ዊዝ አውት ቦርደርስ (ድንበር የለሽ ሐኪሞች ) ድንገተኛ ክፍል ሃላፊ የሆኑት ማሪ ካርመን ቪኖልስ “እጅግ በጣም አስቸኳይ ፍላጎት አለ – ሰብአዊ እርዳታን ለማፋጠን በእንግሊዝኛ ምን ተጨማሪ ቃላትን መጠቀም እንዳለብኝ አላውቅም – እኛ አሁን በምንነናገርበት ጊዜ በየቀኑ ህዝቡ እየሞተ ነው ፡፡” ሲሉ ለአሶሺዬትድ ፕሬስ ገልፀዋል

ነገር ግን የጦርነቱ መቀጠል ፣ የአንዳንድ ባለሥልጣናት ተቃውሞ እና የደረሰው ከፍተኛ ጥፋት የምግብ አቅርቦት ጥረቱ በሚፈለገው ልክ እንዳይሆን እንቅፋት ሆነዋል፡፡ ለ 4.5 ሚሊዮን ሰዎ

ች 15 ኪሎግራም ራሽን ለመላክ ከ 2,000 በላይ የጭነት መኪኖች እንደሚያስፈልጉ  የስብሰባው ቃለ ጉባኤ ያሳያል።

እ.አ.አ. በ 1980 ዎቹ  በኢትዮጵያ ተከስቶ የነበረው ረሃብ ምስሎች ዓለም አቀፋዊ ጩኸት ካስከተሉ አስርት ዓመታት በኃላ ኢትዮጵያ በዓለም በፍጥነት እያደጉ ካሉ ኢኮኖሚዎች ውስጥ አንዷ ሆናለች፡፡ ድርቅ ፣ ግጭቶች እና የመንግስት ሁኔታዎችን መካድ ትግራይ ላስተናገደችው እና 1 ሚሊዮን የሚገመት ሰዎችን ገድሏል ለሚባለው ረሃብ አስተዋጽኦ አድርጓል ። 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (እ.ኤ.አ.) በህዳር ወር በጦር ኃይላቸው እና የተግራይ ክልል መንግስት መካከል ጦርነትን መጀመሩን ባወጁ ጊዜ 5 ሚሊዮን ያህል የህዝብ ብዛት ያለው የትግራይ ክልል በአንበጣ ወረርሽኝ በመጠቃቱ የምግብ ዋስትና ችግር አጋጥሞት ነበር። የትግራይ መሪዎች ለሦስት አስርት ዓመታት ያህል ኢትዮጵያን ተቆጣጥረው የነበረ ቢሆንም አቢይ አህመድ ስልጣን ከተቆናጠጠ እና  በ 2019 የኖቤል የሰላም ሽልማት ያስገኙለትን ማሻሻያዎችን ካስጀመረ በኋላ ተገለው ቆይተዋል::

በጦርነቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለዋል። ከሃምሳ ሺህ በላይ የሚሆኑት ወደ ሱዳን የተሰደዱ ሲሆን አንድ ዶክተር አዲስ መጤ ስደተኞች ላይ የረሃብ ምልክቶች በብዛት እንደሚታዩ ተናግረዋል።  ሌሎች አሁንም በረሃ ውስጥ ተሸሽገዋል፡፡ በቅርቡ ከትግራይ የወጣች አንዲት ሴት ከብቶች ፣ ፍየሎች እና ማጨድ የቻሉትን እህል ይዘው ከመጡ ሰዎች ጋር በዋሻ ውስጥ እንደቆየች ገልፃለች ፡፡

የአዲግራት ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ጳጳስ በላኩት ደብዳቤ “በጦርነቱ መዘዝ እና በምግብ እጦት ሰዎች ሲሞቱ መስማት የየዕለት እውነታ ነው” ሲሉ ገልፀዋል፡፡

የተመጣጠነ ምግብ እጥረትን በማከም ረገድ ወሳኝ የሆኑ ሆስፒታሎችና ሌሎችም ጤና ጣቢያዎች ወድመዋል ፡፡ በገቢያዎች ውስጥ ምግብ “አይገኝም ወይም እጅግ ውስን ነው” ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገልፅዋል።

ምንም እንኳን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኅዳር ላይ ሰራዊታቸው ድል መቀናጀቱን ቢያበስሩም ወታደራዊ እና ሌሎች አጋዥ ተዋጊዎቻቸው ለቀድሞው የክልሉ ባለስልጣናት መራራ ጠላት ከሆኑት የጎረቤት ኤርትራ ወታደሮች ጋር አሁንም ንቁ ሆነው በትግራይ ውስጥ ይገኛሉ ፡፡

ፍርሃት ብዙ ሰዎች ወደ ውጭ እንዳይወጡ አድርጓቸዋል፡፡ ሌሎች ደግሞ ይሸሻሉ፡፡ የትግራይ አዲስ ባለሥልጣናት ከ 2 ሚሊዮን በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን ተናግረዋል ፣ የአሜሪካ መንግሥት የሰብዓዊ ዕርዳታ ቢሮ ይህንን ቁጥር “አስደንጋጭ” ብሎታል፡፡ የተባበሩት መንግስታት እርዳታ የደረሰላቸው ሰዎች ቁጥር “እጅግ ዝቅተኛ” ነው ብሏል።

የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት ሬድዋን ሁሴን በትግራይ ያሉ ባልደረቦቻቸው ስላስተላለፉት የረሀብ ማስጠንቀቂያ አስተያየት እንዲሰጡ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ አልሰጡም ፡፡

በኤርትራ አቅራቢያ፣ በሰሜን ሽሬ አካባቢ እጅግ የከፋው ጦርነት የተካሄደበት ቦታ ሲሆን በአካባቢው እጃቸው ከተለካ ሕፃናት ውስጥ እስከ 10% የሚሆኑት ለከባድ አጣዳፊ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት መመርመሪያ መስፈርት ያሟሉ ሲሆን በርካታ ሕፃናትም ተጠቂ መሆናቸውን የተባበሩት መንግስታት  ምንጭ አስታውቋል፡፡ በርካታ የሰብዓዊ እርዳታ ሠራተኞች ላይ የተጋረጠውን የተደራሽነት አደጋ በመግልፅ መረጃ ሰጪው ማንነታቸው እንዳይገለጥ ጠይቀዋል፡፡

በሽሬ ከተማ አቅራቢያ ባለፉት ዓመታት ከኤርትራ የተሰደዱ ወደ 100,000 የሚጠጉ ስደተኞችን የሚይዙ ካምፖች ይገኛሉ፡፡ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ ሀሙስ እንዳሉት “ወደ ከተማ የገቡት ሰዎች ተዳክመዋል ማቅረብ ያልተቻለ እርዳታ በመለመን ላይ ናቸው” ብለዋል፡፡

ምግብ ዒላማ ሆኖ ቆይቷል፡፡ በዩናይትድ ኪንግደም የተቋቋመ የጥናት ቡድን የሽሬ አካባቢን የሳተላይት ምስሎችን በመተንተን በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች መጠለያ ግቢ ውስጥ ያሉ ሁለት የዓለም ምግብ ፕሮግራም የመጋዘን ሕንፃዎች ተለይተው “ተደምስሰዋል”፡፡ የዲኤክስ  ኦፕን ኔትወርክ በማን እንደተደመሰሱ መለየት ባይችልም ቅዳሜ አዲስ ጥቃት መመዝገቡን ዘግቧል ፡፡

የግንኙነት መስመሮች ደካማ በመሆባቸው እና ጋዜጠኞች ከአካባቢው እንዲዘግቡ ስላልተፈቀደላቸው በትግራይ ውስጥ የሚፈጠሩ ክስተቶችን ማረጋገጥ እና ማስረጃ ማሰባሰብ እጅግ ፈታኝ ነው።

በአዲግራት ፣ በአድዋ እና በአክሱም ከተሞች “በደረስንባቸው ቦታዎች ሲቪሎች ላይ የሚደርሰው ጉዳት እጅግ በጣም ከፍተኛ ነው” ሲሉ የድንበር የለሽ ሐኪሞች የድንገተኛ ክፍል ባለስልጣን ቪኖሌስ ገልፀዋል፡፡ ውጊያን እና የጤና አገልግሎት እጥረቱንም ጠቅሰዋል፡፡ ረሃቡ “በጣም አሳሳቢ ነው” የውሃ እጥረትም ከፍተኛ ነው፡፡ ከ 140,000 በላይ ነዋሪ ያላት አዲግራት ከተማ ውስጥ ከ 21 የውሃ ጉድጓዶች መካከል አሁን የሚሰሩት ሁለቱ ብቻ በመሆናቸው ሰዎች ከወንዝ ውሃ እንዲጠጡ ተገደዋል፡፡ የንፅህና ጉድለተም በሽታን ይስከትላል፡፡ ቪኖሌስ “ከከተማው 10 ኪ.ሜ ያህል(6 ማይል) ርቆ ለወጣ የአደጋው ሙሉ ገፅታ ይታያል” ሲሉ ተናግረዋል፡፡ 

ያለ ምግብ የሰብአዊ እርዳታ ሠራተኞች የችግሩን መጠን ለመለካት ይቸገራሉ፡፡ በኢትዮጵያ የ “Action Against Hunger” ዳይሬክተር የሆኑት ፓኖስ ናቭሮዚዲስ “ከዋና አውራ ጎዳናዎች መጓዝ ባለመቻሉ አሁንም ልናገኛቸው ያልቻልናቸው ሰዎች ሁኔታ እንዴት የከፋ ሊሆን እንደሚችል ጥያቄ ያስነሳል” ብለዋል፡፡

ከግጭቱ በፊት የኢትዮጵያ ብሄራዊ አደጋ አስተዳደር አካል አንዳንድ የትግራይ ወረዳዎችን የምግብ ዋስትና እጥረት በመኖሩ ለእርዳታ ቅድሚያ ሰጥቷቸው ነበር ፡፡ ናቭሮዚዲስ እንዳሉት አንዳንዶቹ ቀድሞውኑ ከፍተኛ የሆነ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት የነበረባቸው ከሆነ ቀውሱ ከጀመረ ሁለት ወር ተኩል በኃላ በሺዎች የሚቆጠሩ ሕፃናት እና እናቶች አፋጣኝ እርዳታ እንደሚፈልጉ መገመት አያዳግትም ብለዋል፡፡

በአሜሪካ በገንዘብ የሚደገፈው እና የሚተዳደረው የረሃብ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ሲስተምስ ኔትወርክ እንዳለው በማዕከላዊ እና ምስራቃዊ ትግራይ ክፍሎች ከርሀብ በታች በሆነ የአስቸኳይ ጊዜ ምዕራፍ 4 ውስጥ እንደሚገኙ ግምት አለ፡፡የሚቀጥሉት ወራቶች በጣም ወሳኝ ናቸው ሲሉ በኢትዮጵያ የካቶሊክ የእርዳታ አገልግሎቶች ተወካይ ጆን ሹምላንስኪ ተናግረዋል፡፡  ቡድናቸው እስካሁን ድረስ ለ 70 ሺህ ይህል የትግራይ ሰዎች የሶስት ወር የምግብ አቅርቦት መስጠቱን ተናግረዋል ፡፡

ተዋጊዎች ረሃብን እንደ መሣሪያ ይጠቀማሉ ወይ ለሚለው ለእርዳታ ሰጪ ሰራተኞች በጣም አሳሳቢ ለሆነው ጥያቄ ሹምላንስኪ በኢትዮጵያ የመከላከያ ኃይል እና ፖሊስ ውድቅ ያደረጉት ሲሆን ሌሎች ጋር ያለውን እንደማያውቁ ተናግረዋል፡፡ “እነሱም በቂ ምግብ የላቸውም ብዬ አስባለሁ” ብለዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Exit mobile version